The Constitutionality of Proc.97/98
የአዋጅ ቁጥር 97/90 ሕገ- መንግስታዊ ቅቡልነት ብርሐኑ በየነ ብርሐኑ (LL.M, LL.B) Email - [email protected] ፣ [email protected] 1. መግቢያ አዋጅ ቁ.97/90 [1] ባንኮች ብድር ሲሰጡ የመያዣ መብት ያቋቋሙበትን ንብረት የፍ/ቤት ይሁንታ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው ለመሸጥ እና ከሽያጩ የተገኘውን ገንዘብ ለብድሩ መክፈያነት ለማዋል እንዲችሉ ሥርዐት የዘረጋ አዋጅ ነው፡፡አዋጁ ባንኮች ሽያጩን ለማከናወን መከተል ያለባቸውን ዝርዝር የአፈጻጸም ሥነ-ሥርዐቶችን [2] የያዘ ሲሆን ባንኮች ከፍ/ቤት ውጭ መያዣ ሊሸጡ የሚችሉት በማናቸውም ሁኔታ ሳይሆን ብድሩ ሳይከፈል ሲቀር ሽያጩን እንዲያደርጉ ከተበዳሪዎች/አስያዦች ጋር ቀድሞ በተደረገ ስምምነት መብት ከተሰጣቸው ብቻ መሆኑን ይደነግጋል [3] ፡፡ የአዋጁ ዐላማ በአጭሩ ባንኮች ብድር ለማስመለስ ወደፍ/